Fana: At a Speed of Life!

በባቲ ካሳጊታ ግንባር የጠላት ምሽግ ተሰበረ

 

ሰበር ዜና

በባቲ ካሳጊታ ግንባር የጠላት ምሽግ ተሰበረ፣ አምባው ተደፈረ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባቲ ካሳጊታ ግንባር ያለ የሌለ ዐቅሙን ሰብስቦ የመጣው የጠላት ኃይል ለወሬ ነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ ተደመሰሰ።

የጠላት አርሚ 4 የተባለው ሠራዊት ከነ ተደራቢ ኃይሉ ሳምንት ሙሉ ሲቀጠቀጥ ከርሞ በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ በፈጀ ውጊያ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊትና በአናብስቱ የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ አከርካሪው ተሰብሯል።

በዚህ አስደናቂ ውጊያ ጀግኖቹ ባደረጉት ተጋድሎ፣ ጠላት ሲተማመንባቸው የነበሩትን ሁለት ስትራቴጂካዊ ተራሮች ምሽጎቹን በመስበር ተቆጣጥሯል።

በዚህ ሰሞን ዉጊያ ጠላት ሚሌ እገባለሁ በሚል የሰበሰባቸው በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹና ጀሌዎቹ ተደምስሰውበታል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማርከዋል፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፣ በርካታ ስናይፐሮችና መትረየሶች ተማርከዋል። ጠላት በዚህ ግንባር ከደረሰበት ውድመት የዛሬው እጅግ ዘግናኝ መሆኑ ታውቋል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.