Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ጅማ አባ ጅፋር እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሣምንት የመክፈቻ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋር እና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል።

ረፋድ ላይ በተካሄደ ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋ አርባምንጭ ከተማን 2 ለ 1 በመርታት ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል፡፡

የጅማ አባ ጅፋር ጎሎችን አስጨናቂ ፀጋየ እና እዮብ አለማየሁ ሲያስቆጥሩ÷ የአርባ ምንጭ ከተማን ብቸኛ ጎል አሸናፊ ኤሊያስ ማስቆጠር ችሏል፡፡

ቀትር ላይ በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ጨዋታውን ድሬዳዋ ከተማ በሄኖክ አየለ ጎል መምራት ቢችልም አቡበክር ናስር ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ቡናማዎቹ ባለ ድል ሆነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.