Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ክልል ለመከላከያ ሠራዊት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ተገብቷል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከመንግሥት ሠራተኞችና ከባለሀብቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልሉ ፀጥታ ኃይል ለመደገፍ 11 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱ ተገለጸ።
በክልሉ የሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ሰጪ አብይ ኮሚቴ የስራ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት የሀገር መከላከያ ሰራዊትንና የክልሉ ፀጥታ ኃይል ለመደገፍ ከክልሉ መንግሥት ሰራተኞችና ባለሀብቶች 11 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ቃል መገባቱን አስታውቋል።
ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ምላሽ በመስጠት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመቀላቀል ለወሰኑ ለክልሉ ወጣቶች ክብር እንደሚገባቸውም ኮሚቴው ገልጿል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የአብይ ኮሚቴው ሰብሳቢ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የድጋፍ ሥራው ከተያዘው ዕቅድ በላይ እየተከናወነ ነው ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.