Fana: At a Speed of Life!

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 26 እስከ 28 እንደሚሰጥ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 26 እስከ 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንደማሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ።

በቢሮው የስርዓተ-ትምህርት ፤ የትምህርት ተቋማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀሰበላ አዜን እንደገለጹት፣ ቢሮው በክልሉ በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየሰራ ነው።

ፈተናው በ307 የክልሉ የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ገልጸው፤ የትምህርት አመራሮች፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮችና የወላጅ ተማሪ ህብረት ተወካዮች ተፈታኝ ተማሪዎችን በስነ-ልቦና እንዲዘጋጁ በማድረግ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

አቶ ሀሰበላ አክለውም፣ በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው የፀጥታ ችግር፣ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው ፕሮግራም መሠረት ፈተናውን ለመስጠት አስቸጋሪ እንዳይሆን ወላጆችና ተማሪዎች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.