Fana: At a Speed of Life!

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህላዊ የማዕድን ኩባንያዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ ይደረጋል-ኢ/ር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባህላዊ የማዕድን ኩባንያዎች ያሉበትን ደረጃ ጎበኙ፡፡

በጉብኝቱ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ኩባንያዎቹ ለስራቸው እንቅፋት የሆኑባቸው ጉዳዮች መፍትሄ እያገኙ ነው ያሉት ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ በቀጣይም በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡ እናደርጋለን ብለዋል።

በአሁኑ ጊዜም በክልሉ በማዕድን ልማት ላይ የተሰማሩ ከጸጥታ ስጋት ተላቀው ስራቸውን እንዲሰሩ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ይገኛሉ ብለዋል ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፡፡

የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ ጠዋት ነው ለጉብኝት አሶሳ ከተማ የገቡት፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.