Fana: At a Speed of Life!

በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በጉዋንዡ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ልኡካን ከጂያንግዢ ክልል አስተዳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በጉዋንዡ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ልኡካን ከጂያንግዢ ክልል አስተዳደር ጋር ተወያዩ፡፡
በቻይና የኢፌዴሪ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የተመራው ልዑክ ከዋና አስተዳዳሪ ዪ ሊያንሆንግ ጋር ተወያይቷል፡፡
በማንቻንግ ከተማ በተካሄደው ውይይት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር መክረዋል፡፡
ልዑኩ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት በግዛቷ እያደረገ ሲሆን ከግዛቷ የግብርናና ቱሪዝም ምክትል ዳይሬክተር ሁዋንግ ዚዎሮንግ ጋርም መክሯል፡፡
በቆይታቸውም የቱሪዝም ትብብርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ተወያይተዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.