Fana: At a Speed of Life!

በብሔራዊ ደህነንት ምክር ቤት በተዘጋጀ የምርጫ ፀጥታ ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 18 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በተዘጋጀው አገር አቀፍ የምርጫ ፀጥታ ዕቅድ ላይ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት ተወያዩ።
ዕቅዱ የተዘጋጀው በተያዘው ዓመት የሚካሄደውን አገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ፣ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
በውይይቱ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ በሚመሩት የምርጫ ፀጥታ ዕቅድ የምክክር መድረክ የፌዴራልና የክልል ባለድርሻ አካላት ታድመዋል።
እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የጠቅላይ አቃቤ ሕግና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊዎች እንዲሁም የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ርዕሳነ መስተዳድርሮችና ከንቲባዎች፣ የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊዎች፣ ፖሊስ ኮሚሽነሮችና ጠቅላይ አቃቤያነ ሕጎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ወይዘሪት ብርቱካን ኢትዮጵያ በ2013 ዓ.ም ለምታካሂደው አገር አቀፍ ጠቅላላ ምርጫ የምርጫ ፀጥታ ግብረ ሃይል መቋቋሙን ተናግረዋል።
የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው በአገራዊ የምርጫ ጸጥታ ዕቅዱ መሰረት ክልሎች የራሳቸው ዕቅድ ያላቸው በመሆኑ በዚሁ ላይ በጋራ ለመስራት መነጋገር በማስፈለጉ እንደሆነም ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.