Fana: At a Speed of Life!

በብሪታኒያ በዚህ ሳምንት 3 ሕጻናት በኮረና ቫይረስ ተይዘዋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 10፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሪታኒያ በዚህ ሳምንት 3 ሕጻናት በኮረና ቫይረስ ተይዘዋል።

በቫይረሱ የተያዙት ህፃናት አንደኛው በለንደን ከተማ የተወለደ ጨቅላ ሕፃን፣ በማንቸስተር የዘጠኝ ወር ሕፃን እና በኖርፎልክ ውስጥ የሚኖር የአንድ ዓመት ልጅ መሆናቸው ተነግሯል።

የኮረና ቫይረስ በየትኛውም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የሚያጠቃ ሲሆን÷ ሕፃናት ከአዋቂዎች ያነሰ በቫይረሱ የመያዝ እድል እንዳላቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከዚያም ባለፈ በቫይረሱ የተያዙ ሕፃናት አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ምልክቶች ብቻ እንደሚታይባቸው ነው የተገለፀው።

ነገር ግን ተመራማሪዎች የልጆች እና አዋቂዎች አካላት በኮሮና ቫይረስ ለምን የተለያየ ምላሽ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተቸግረዋል።

የቫይረሱ ዋና ማዕከል በነበረችው ቻይና በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 2 ነጥብ 4 ከመቶ የሚሆኑት ልጆች ብቻ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥም 0 ነጥብ 2 ከመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ከባድ ህመም ማሳየታቸው ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ ዴይሊ ሜይል

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.