Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት ብቻ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ተፈፀመ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በቦሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው መርሃ ግብር ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ ተካሄደ።

“ግድቡ የእኔ ነው” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ስነ ስርዓት የክፍለ ከተማውና የወረዳ አስተዳደር አመራሮች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ አርሶ አደሮች እና ሌሎች ነዋሪዎች የቦንድ ግዢ ፈፅመዋል።

በዚህም በዛሬው ዕለት ብቻ ብር የ4 ሚሊየን 798 ሺህ 163 ብር የቦንድ ግዢ ፈጽመዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በመርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር “ይህ የቦንድ ግዢ በዛሬው ዕለት ሲካሄድ በውስጣችን የነበሩ መጥፎ አስተሳሰቦችን በመንቀል አዲስ ችግኝ በተከልንበት ዕለት በመሆኑ የተለየ ቦታ ይሰጠዋል” ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.