Fana: At a Speed of Life!

በቫሌንሺያ በተደረገው የማራቶን ውድድር ጫሉ ዴሱ እና እታገኝ ወልዱ ሁለተኛ ወጡ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በስፔን ቫሌንሺያ በተደረገው የማራቶን ውድድር በውድድሩ ላይ የተሳተፉት አትሌት ጫሉ ዴሱ እና እታገኝ ወልዱ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

አትሌት ጫሉ ዴሱ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በሆነ ሰዓት እንዲሁም አትሌት እታገኝ ወልዱ ደግሞ 2 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድራቸውን በሁለተኝነት አጠናቀዋል።

በውድድሩ አትሌት አበበ ነግዎ አምስተኛ፣ ክንዴ አጣነው ሰባተኛ እንዲሁም ሄርፓሳ ነጋሳ አሥረኛ በመሆን ጨርሰዋል።

በሴቶች ደግሞ በየኑ ደገፉ ሦስተኛ፣ ረሂማ ቱሳ አራተኛ፣ አዝመራ ገብሩ ስድስተኛ፣ አዳነች አንበሳ ሰባተኛ እና መሰረት ድንቄ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘው ማጠመናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በዚሁ የማራቶን ውድድር ኬንያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታ አሸናፊ ሆነዋል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.