Fana: At a Speed of Life!

በተለያየ ጊዜ ስርቆት ፈጽመዋል የተባሉ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያየ ጊዜ ስርቆት ፈጽመዋል የተባሉ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ በልዩ ልዩ ጊዜ የተሰረቁ 117 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ማስመለሱን ጠቁሞ÷ በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸው 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መገናኛ አካባቢ ዘፍመሽ የገበያ ማዕከል ውስጥ ከሚገኝ አንድ የንግድ ቤት ላይ የተፈፀመን የስርቆት ወንጀል መነሻ በማድረግ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ፥ በልዩ ልዩ ጊዜ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰረቁ 117 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ባለ 24፣ 32 እና 42 ኢንች ሦስት ቴሌቪዥኖች፣ 6 ፕሌይ ስቴሽኖች እና 1 ፕሮጄክተር ማስመለሱን ነው የአዲስ አበባ ፖሊስ የገለጸው፡፡
በዚህ የወንጀል ድርጊት ተሳትፎ ያላቸውና የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የጥበቃ ሰራተኞችና የተሰረቀ እቃ የሚገዙ ተቀባዮች በድምሩ 21 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.