Fana: At a Speed of Life!

በተለያየ ግንባር እየተገኙ ላሉ ድሎች የሎጅስቲክ አቅርቦቱ ድርሻ ከፍተኛ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር ጠላት የሆነውን የህወሓት ቡድን ለመደምሰስ ልዩ ልዩ ሎጀስቲኮች በተገቢው መንገድ መቅረባቸው እየተገኘ ላለው ድል ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የአማራ ክልል ልዩ ኃይል የደብረ ዘቢጥ ግንባር የሎጅስቲክ አቅርቦት ኃላፊ ኮሎኔል አለባቸው ብዙነህ ገለፁ፡፡
የሎጅስቲክ አቅርቦት በተገቢው መንገድ መሟላቱ በየግንባሩ ከፍተኛ ድል እንዲመዘገብ ማስቻሉን ኮሎኔል አለባቸው ተናግረዋል፡፡
ለዚህም በደብረ ዘቢጥ ግንባር ውጤታማ ተግባር እንዲገኝ ማስቻሉ ማሳያ ነውም ብለዋል፡፡
በአንድ ጦርነት ላይ የግብዓት አቅርቦት ከፍተኛ ድርሻ በመጫወት ጠላትን ለማንበርከክ ያስችላል ሲሉም ነው የደብረዘቢጥ ግንባር የሎጅስቲክ አቅርቦት ኃላፊው የተናገሩት፡፡
ኮሎኔል አለባቸው ብዙነህ አክለውም የሎጂስቲክ እጥረት እንዳይከሰት ክትትል በማድረግ እያሟሉ እንደሆነ አስረድተዋል።
በቀጣይ የጠላት ኃይል ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ በሎጅስቲክ ክፍሉ ችግር እንዳይገጥም እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
ከተተኳሽ መሳሪያዎች ውጪ ማሕበረሰቡ ለሠራዊቱ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ድጋፍ በማድረግ ትልቅ አቅም ፈጥረውልናልም ብለዋል፡፡
በቀጣይም ይሄ የሽብር ቡድን ከኢትዮጵያ ምድር እስኪጠፋ ድረስ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.