Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን የሚገልጽ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ አካባቢዎች ለአገር መከላከያ ሰራዊት አጋርነትን የሚገልጽ የድጋፍ ሰልፍና የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል።
በአዲስ አበባ ፣በጋምቤላ ፣ በአሶሳ ፣ በወልቂጤ፣ በሀረሪ፣ በሀላባ እና በሌሎች ከተሞች ለመከላከያ የድጋፍ ሰልፍ እና የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ውድድር ተካሂዷል።
በሀላባ ከተማ ” እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ ” በሚል መሪ ቃል የ5ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርና 172 ሰንጋና 88 በግና ፍየል ለመከላከያ ሰራዊት ተበርክቷል።
በፕሮግራሙ ላይ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ተገኝተው ደም መለገሳቸውን ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.