Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ የአማራ ከተሞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና አሸባሪውን ህውሃትን በማውገዝ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የአማራ ከተሞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እና አሸባሪውን ህውሃትን በማውገዝ ሰልፎች ተካሂደዋል።
በዚህም በጎንደር፣ በእንጅባራ እና በደብረ ብርሃን ከተማ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ዛሬ በደብረ ብርሃን ከተማ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ የቀድሞ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ለሀገር ህልውና ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመዉ ታላቅ ክህደትና በንጹሃን ላይ ያደረገው የዘር ጭፍጨፋ ይቅር የማይባል መሆኑን ነው ሰልፈኞቹ የገለጹት።
ለሀገር አፍራሹ ቡድን በመወገን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ እያሳደሩ ያለውን ጫና በጋራ መከላከል እንደሚገባም የቀድሞ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት አሳስበዋል።
የድጋፍ ሰልፉ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ እንዲሁም ሕዝባዊ ሠራዊት ድጋፍን ለመግለጽ ነው መካሄዱን አሚኮ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.