Fana: At a Speed of Life!

በተቀናጀ የከተማ ውበት፣ የአረንጓዴ ልማት እና የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ስራ የሚፈጠረው የስራ እድል በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ መቀጠል አለበት- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተቀናጀ የከተማ ውበት፣ የአረንጓዴ ልማት እና የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ ስራ የሚፈጠረው የስራ እድል በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ዘርፎች ከ28 ሺህ በላይ ዜጎች አዲስ የስራ እድል ለመፍጠር በታቀደው መሠረት የሰው ልየታ እና የቦታ ዝግጅት በመጠናቀቁ ከረቡዕ ጀምሮ በሁሉም የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ስልጠና ይጀመራል ተብሏል ።
አዲስ የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ዜጎች ስራ ለማስጀመር የቅድመ ስልጠና እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የማዘጋጃ ቤታዊ ዘርፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እና የሚመለከታቸው አስተግባሪ ተቋማት ጋር ምክክር ተካሄዷል ።
በምክክር መድረኩ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ÷ የፊታችን ጥር ወር በሚጀመረው በተቀናጀ የከተማ ውበት፣ አረንጓዴ ልማት እና በደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብ በሚኖሩበት አካባቢ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ዜጎች የሚያከናውኑት ተግባር በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
የሚፈጠረው የስራ እድል ግልጽነት የሰፈነበት እንዲሆን እና ከ50 በመቶ በላይ ሴቶች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።
ለዚህ የስራ እድል ፈጠራ የሚውል ስራ ማስኬጃ የከተማ አስተዳደሩ 200 ሚሊየን ብር በጀት መመደቡንም ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.