Fana: At a Speed of Life!

በተያዘው በጀት አመት 350 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን ለመመዝገብና ለማረጋገጥ ታቅዷል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 በጀት አመት 350 ሺህ የመሬት ይዞታዎችን ለመመዝገብና ለማረጋገጥ ማቀዱን የፌደራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ገለፀ ።
ከመሬት መረጃ አያያዝ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል።
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በሚቀጥሉት አስር አመታት በከተማ ልማት ዘርፍ ለመስራት ከታቀዱ ላይ የወጣ የአምስት አመት እስትራቴጂክ እቅድ ላይ ከክልሎች ጋር በመወያየት ወደ ተግባር ለመግባት ያለመ ምክክር በመደረግ ላይ ይገኛል።
የምዝገባ ስራው የመሬት ወረራንና ህገወጥነትን የሚያስቀር እንዲሁም ከመሬት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን የሚፈታ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ ይገባል ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
ባለፋት አምስት አመታትም በ40 ከተሞች 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ይዞታዎችን ለመመዝገብና ለማረጋገጥ አቅዶ 457 ሺህ 907 ይዞታዎችን ማረጋገጥና መመዝገብ መቻሉን ገልፀው ከእቅዱ አንፃር በቂ አለመሆኑን አንስተዋል።
በሌላ በኩል ህዝቡን ግንዛቤ የሚያስጨብጡ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በብርሃኑ በጋሻው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.