Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ35 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበበሳ፣ጥር 17፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቃዊ ቱርክ በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ የአደጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ ባለስልጣን  አስታወቀ።

በደረሰው የመሬት መንቀጥቅጥ  ህንጻዎች የፈራረሱ ሲሆን  በፍርስራሹ ስር የሚገኙትን ሰዎች ለማትረፍት ጠንካራ የሆነ የነብስ አድን ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ለነፍስ አድን ስራው መቆፊሪያዎች ፣ መቦርቦሪያ ፣ ባልዲዎች እና ሌሎች መሳሪያዎች በመጠቀም የነፍስ አድን ስራው እየተከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

ምስራቃዊ ቱርክ ዓርብ ምሽት በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8  በተለካው ርዕደ መሬት ከተመታ በኋላ  31 ሰዎች በኤላዚግ 4 ሰዎች ደግሞ አጎራባች በሆነችው በማላያ  ህይወታቸውን እንዳጡ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ባለፈ ከ1 ሺህ 600 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የቱርክ የአደጋ እና የአስቸኳይ ጊዜ ባለስልጣን አስታውቋል።

በብዛት የነፍስ አድን ስራው መጠናቀቁን የገለፁት የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሱሌማን ሶይሉ  አሁንም በፍርስራሽ ውስጥ የሚገኙት ስድስት ሰዎች ለማዳን የአደጋ ጊዜ ሙያቶች እየሰሩ ይገኛል ብለዋል።

በአደጋው የተጎዱ ሰዎች ድጋፍ  እንደሚደረግላቸው ገልፀው ÷ አሁንም የአደጋ ተጋላጭንት ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ ወደ ፈረሱት  ሕንፃዎች እንዳይመለሱም አሳስበዋል ፡፡

የአካባቢና የከተማ ልማት ሚኒስትሩ ሙራራት ኩር በበኩላቸው በአደጋው በበርካታ ግዛቶች ህንፃዎችን እንደተጎዳ  የገለፁ  ሲሆን ÷ 12 ህንፃዎች  በአደጋው ወድያውኑ ወድመዋል    ብለዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ፋራቲቲን ኮካ ÷104 ሰዎች በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 13 ቱ የቅርብ ክትትል እየተደረገላቸው  እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

አያይዘውም ወደ ችግሮች ወደ ተከሰቱባቸው  አውራጃዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኛ ችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን የነፍስ አድን ስራውን እንዲደግፉ መላካቸውን ጠቁመዋል፡፡

በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለተፈናቃዮች ዜጎችም የመጠለያ ድንኳኖች ፣ አልጋዎች እና ብርድ ልብሶች መሰጠታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ታይፕ ኤርዶኻን  አደጋው በደረሰበት በኤላዚግ እና ማላያ  አውራጃዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ÷ ለተፈናቃዮች በብረት የተገነቡ ቤቶች በአካባቢዎቹ በፍጥነት እንደሚገነቡ  ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

 

ምንጭ፡-ሮይተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.