Fana: At a Speed of Life!

በቱርክ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ 20 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ 20 ሰወች መሞታቸው ተነገረ።

በምስራቅ ቱርክ በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪ ከ900 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውም ነው የተነገረው።

በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 8 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጥ ወደ 30 የሚጠጉ ህንጻዎች ማፍረሱን ፖሊስ አስታውቋል።

የሃገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሱሌይማን ሶይሉ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ የተቀበሩ 30 ሰዎችን እየፈለጉ ነው ብለዋል።

በፈረንጆቹ 1999 በሰሜን ምዕራብ የሃገሪቱ ክፍል የደረሱ ሁለት የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋዎች ለ18 ሺህ ሰዎች ህልፈት ምክንያት መሆናቸውን ዘገባዎች ያመላክታሉ።

ቱርክ በአቀማመጧ ምክንያት በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ ታስተናግዳለች።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.