Fana: At a Speed of Life!

በቱኒዚያ ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ሰጥማ 17 ስደተኞች ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱኒዚያ ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሞከሩ ስደተኞችን የያዘች ጀልባ ሰጥማ ቢያንስ 17 ስደተኞች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡
ስደተኞቹ በቱኒዚያ የባህር ዳርቻ ሜዲትራንያንን አቋርጠው ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ ነው ለህልፈት የተዳረጉት፡፡
ሕይወታቸው ካለፉ ሰዎች መካከልም አብዛኛዎቹ ከባንግላድሽ የመጡ ናቸው ተብሏል ፡፡
ከ 160 በላይ ስደተኞችን ደግሞ የቱኒዚያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች እንደታደጓቸው ተነግሯል ፡፡
የሰጠመችው ጀልባም ከተለያዩ አገራት የመጡ ስደተኞችን ጭና ከሊቢያ የዙዋራ ወደብ መነሳቷ ታውቋል ፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.