Fana: At a Speed of Life!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁናዊ ሁኔታ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና ሃገራዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አሁናዊ ሁኔታ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና ሃገራዊ ንቅናቄ ለመፍጠርያለመ ውይይት በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ተካሄደ።

“የህልውናችን ፕሮጀክት” በሚል እየተካሄደ ያለው ውይይት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ ውሃ ሙሌትና በተለያዩ አካላት እየተንጸባረቀ ባለው አቋም ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመያዝና ሃገራዊ ንቅናቄ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ውይይቱን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በንግግር ከፍተዋል።

በውይይቱ በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በርዕሰ ጉዳዩ ላይ መነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል።

የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የውሃ ጥናትና ምርምር፣ ዓለም አቀፍ ስምምነትና ግድቦች ግንባታ መስኮች ላይ የሚሰሩ ምሁራንና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.