Fana: At a Speed of Life!

በ“ቴክስት ሪኮግኒሽን” ቴክኖሎጂ ላይ በትብብር ለመሥራት ከቻይናው ዩኒቨርሲቲ ጋር ሥምምነት ተደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሁዌዦንግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በ“ቴክስት ሪኮግኒሽን”ቴክኖሎጂ ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ስምምነቱ በቴክስት ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ላይ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ትብብር እንዲኖር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በስምምነቱ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በዚህም በትምህርት እና ቴክኖሎጂ ትብብር ላይ በጥምረት ለመስራት እንደሚያስችል በስምምነቱ ተገልጿል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሁዌዦንግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አፍሪካዊ ጽሁፎችን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማግባባት የሚያስችለውን ዳታ የማልማት ተግባር ያከናውናል መባሉን ከኢኒስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.