Fana: At a Speed of Life!

በትንፋሽና በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በትንፋሽና በንክኪ የሚተላለፉ በሽታዎች በየትኛውም ቦታ በቀላሉ ከሰው ወደ ሰው የመዛመት አቅም አላቸው።
እንደ ጉንፋን፣ ኢንፍሉዌንዛን ጨምሮ ከሰሞኑ የዓለም ስጋት የሆነው ኮሮና ቫይረስ ይጠቀሳሉ።
የህክምና ባለሙያዎችም እነዚህ በሽታዎች ለመከላከል ያግዛሉ ያሏቸውን ምክረ ሃሳቦች አቅርበዋል፤ጭንቀትን መቀነስ በሚጨነቁበት ጊዜ ሰውነት የጭንቀት ሆርሞኖችን ይፈጥራል፤ ይህ ደግሞ በሰውነት በሽታን የመከላከል አቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል።
ይህ እንዳይሆን ደግሞ ራስን አለማስጨነቅና ዘና ያለ ስሜት የሚፈጥሩ አማራጮችን መጠቀም።
እረፍት ማድረግ
እረፍት ማድረግ ሰውነት ራሱን እንዲያድስና የተሻለ ብርታት እንዲያገኝ ይረዳዋል።
ድካም ሲሰማ አለማረፍ ሰውነት ጥንካሬውን እና በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያጣ ስለሚያደርግ በቀላል በሽታዎች የመጠቃት እድልን ያሰፋል።
ከዚህ አንጻርም እረፍት ማድረግ ይመከራል።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጎልበት ከሚረዱ ነገሮች ውስጥ አንዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ነው።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስናድርግ መጠንቀቅ አለብን ምክንያቱም ጫና ያለው የአካል እንቅስቃሴ በሰውነት ላይ ውጥረት ስለሚፈጥር በሰውነት በሽታ የመቋቋም ጥንካሬ ላይ ችግር ያስከትላል።
ከዚህ አንጻርም ጫና ያልበዛበት ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ይገባል።
አመጋገብን ማስተካከል
ባለሙያዎች የሰውነትን በሽታ የመከላከያ አቅምን ለማሳደግ አመጋገብን ማስተካከል እንደሚገባ ይመክራሉ።
በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ምግቦች፣ ፍራፍሬ፣ ነጭ ሽንኩርት፣ አበባ ጎመን እና እንደ ሰላጣ ያሉ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነው።

በተጨማሪም በቫይታሚን ቢ፣ ዲ እና ዚንክ እና ማዕድናት የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ አስፈላጊ ነው።

ምንጭ፦ psychologytoday.com/intl

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.