Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ለሚገኙ 25 ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች የምግብ ድጋፍ እየቀረበ ነው – የዓለም ምግብ ፕሮግራም

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 25 ሺህ ኤርትራውያን ስደተኞች የምግብ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በትግራይ ክልል በሚገኙ ሁለት የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ለአንድ ወር የሚሆን የምግብ ድጋፍ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም፣ በተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ እና በኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ በኩል መቅረቡ ተገልጿል።

በዚህም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመተባበር በማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ ለሚገኙ 13 ሺህ ኤርትራውያን በ18 ከባድ ተሽከርካሪዎች 250 ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ድጋፍ ቀርቧል ።

በተመሳሳይ በአዲ ሀሩሽ የስደተኞች ጣቢያ ለሚገኙ 12 ሺህ 170 ኤርትራውያን 240 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ እንደተሰራጨ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

የምግብ ድጋፉ በመጠለያ ጣቢያ እንደደረሰ ለስደተኞቹ ተሰራጭቶ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ ላደረገው ትብብር ምስጋና ያቀረቡት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ እና ዳይሬክተር ስቴቨን ዌር ኦማሞ ይህም በሌሎች የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ስደተኞች እንዲቀጥል የመንግስት ትብብር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.