Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍን ለማፋጠን የፀጥታ ሃይሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሊይ አማካሪ ጋአቪን ግርምስታት፣ በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ዳይሬከተር ስቴቨን ዌር ኦማሞ እና የፕሮግራሙ የአስቸካይ ጊዜ ማስተባበሪያ አማካሪ ማርክ ጎርደን ከኢታማዦር ሹሙ ጋር ባደረጉት ቆይታ በትግራይ ክልል በተከሰተው ችግር ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የሰብዓዊ ድጋፍ አሰጣጥን በተመለከተ መክረዋል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ኃላፊዎች በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍን ለማቅረብ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ያለበት፣ አልፎ አልፎ ችግር የሚታይበትና ሙሉ ለሙሉ ችግር ያለባቸው በማለት ለይተው አቅርበዋል።
ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ በጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የህወሃት አሸባሪ ቡድን የፈጸመውን የተቀናጀ ጥቃት ማብራራታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ይህንን ተከትሎ መንግስት የአገርና የህዝብን ሉዓላዊነት ለማስከበር ሲል ወደ ህግ ማስከበር መግባቱንም አስረድተው በአሁኑ ወቅት የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት የማድረግ ስራዎች እየተከናወኑና ለማቅረብም ምቹ ሁኔታ መኖሩንም አረጋግጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.