Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገለጸ።
የኮቪድ-19ን ለመከላከል እንዲያግዝ በመቐለ ከተማ የተጀመረውን ክትባት በትግራይ ክልል ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል፡፡
በጤና ቢሮው የኮቪድ-19 መከላከያ ሃላፊ ዶክተር አርነት አዳነ እንዳሉት÷ ለክትባት አገልግሎት የሚውል 108 ሺህ ዶዝ መድሐኒት ከጤና ሚኒስቴር ለክልሉ ተልኳል።
በዚህም በመቐለ ከተማ በሚገኙ ሁሉም የጤና ተቋማት ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ዜጎች ክትባት መስጠት መጀመሩን ተናግረዋል።
በመቐለ የተጀመረው የክትባት ዘመቻ በሽሬእንዳስላሴ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ፍሬወይኒ፣ ማይጨውና አዲሽሁ ከተሞች በተያዘው ወር ውስጥ እንደሚቀጠል አስታውቀዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ወደ ክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት ተጨማሪ የክትባት መድሐኒት ከጤና ሚኒስቴር እየተጠበቀ እንደሆነ ጠቁመው የክትባት መድሐኒት ማቆያ ፍሪጅ ዝግጅትና የጤና ባለሙያዎች ስልጠና እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በመቐለ ከተማ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ክትባቱ መሰጠቱ ይታወሳል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.