Fana: At a Speed of Life!

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኘች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ጉዳፍ ፀጋዬ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኘች፡፡
በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሃሰን ለኔዘርላንድስ የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ ኬንያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ለሀሃገሯ አስገኝታለች፡፡

በውድድሩ የተሳተፈችው  አትሌት እጅጋየሁ ታዬ አምስተኛ በመሆን ውድድሩን ስታጠናቅቅ አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ  ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን ጨርሳለች፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.