Fana: At a Speed of Life!

በቶኪዮ ኦሊምፒክ በወንዶች መሰናክል ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኘ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 9፡15 በተካሄደው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ሩጫ ውድድር ለሜቻ ግርማ ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

በዚህም ለሜቻ ግርማ  ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ  ሲያስገኝ  ጌትነት ዋለ ውድድሩን በአራተኝት አጠናቋል፡፡

ሞሮኳዊው አትሌት ሶፊያን ኤል ባካሊ ውድድሩን ሲያሸንፍ ኬንያዊው አትሌት ኪገን ቤንጃሚን ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡

አትሌት ለሜቻ ግርማ ያስገኘው የብር ሜዳልያ በ1980 በሞስኮ ኦሊምፒክ አትሌት እሸቱ ቱራ ካስገኘው ሜዳልያ በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡
 
ይህም ከ41 አመታት በኋላ የተገኘ ሜዳልያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.