Fana: At a Speed of Life!

በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ 8:00 ሰዓት የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ ዛሬ ቀን 8:00 ሰዓት ጀምሮ የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በውድድሩ ዮሚፍ ቀጀልቻ፣ ሰለሞን ባረጋ እና በርሁ አረጋዊ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ለማስመዝገብ ውድድራቸውን ያካሂዳሉ፡፡
በተመሳሳይ በሴቶች 5 ሺህ ማጣሪያ እጅጋየሁ ታዬና ሰንበሬ ተፈሪ በምድብ 1 እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋይ በምድብ 2 ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ይወዳደራሉ፡፡
በቶኪዮ ኦሊምፒክ እስካሁን በተካሄዱ ውድድሮች ቻይና 18 ወርቅ፣ 9 ብር እና 11 ነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ቀዳሚ ናት፡፡
ጃፓን በ15 ወርቅ፣ 4 ብር እና በ7 ነሀስ 2ኛ ስትሆን ÷ አሜሪካ ደግሞ 14 ወርቅ፣ 16 ብር አና 11 ነሀስ በማግኘት 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.