Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 41 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 41 መድረሱ ተሰምቷል።

በቅርብ በቻይና ውሃን  ግዛት የተቀሰቀሰው ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አድማሱን በማስፋት በተለየዩ የዓለም ሀገራት ውስጥ መከሰቱ ተነግሯል።

ቫይረሱ አሁን ላይ 10 በሚሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ የተከሰተ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የእስያ ሀገራት መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም በአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣  ጃፓን፣ ታይላንድ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ አውስትራሊያ፣ ማሌዥያ እና በሌሎች ሀገራት መከሰቱ ነው የተነገረው።

ይህን ተከትሎም በርካታ ሀገራት የመተንፈሻ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ ለህልፈት የሚዳርገው ይህ የኮሮና ቫይረስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገባ ከፍተኛ ቅድመ ጥንቃቄ  እያደረጉ ይገኛሉ።

በቻይና እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 41 የደረሰ ሲሆን፥1ሺህ 300 የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸው ተነግሯል።

ምንጭ፦ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.