Fana: At a Speed of Life!

በቻይና በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱ ጾታዎች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በቻይና በተደረገው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ሲያሸንፉ በሴቶች ምድብ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በውድድሩ በወንዶች አትሌት ብርሃን ንባባው ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ8 ደቂቃ ከ16 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ሲያሸንፍ፥ ግርማይ ብርሃኑ ሶስተኛ በመሆን አጠናቋል።

በሴቶች ምድብ ደግሞ አትሌት መዲና ደሜ 2 ሰዓት ከ26 ደቂቃ ከ12 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ስታሸንፍ፥ መሰራ ሁሴን እና አፌራ ጎድፈይ ደግሞ ተከታዮቹ ደረጃዎች ይዘው አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በሜክሲኮ በተካሄደ የማራቶን ውድድር በወንዶች ገዛኸኝ ሁንዴ በ2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ19 ሰከንድ አሸናፊ ሆኗል።

በቱርክ የግማሽ የማራቶን ውድድር እና ስፔን በተካሄደ ሃገር አቋራጭ ውድድርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.