Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የተከሰተው አዲስ ቫይረስ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየተስፋፋ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ውስጥ የተከሰተው አዲስ ተላላፊ ቫይረስ ወደ ተለያዩ ሃገራት እየተስፋፋ ነው።

ቫይረሱ በቻይና በርካታ ግዛቶች የተከሰተ ሲሆን እስካሁን ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

አሁን ላይ ቫይረሱ አሜሪካን ጨምሮ በታይላንድ እና ደቡብ ኮሪያ መስፋፋቱም ነው የተነገረው።

የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃው ይህ ቫይረስ አሁን ካለበት በላይ ሊስፋፋ እንደሚችልም ባለስልጣናቱ አስጠንቅቅዋል።

እስካሁን 440 የቫይረሱ ተጠቂዎች መኖራቸው ተገልጿል።

ቫይረሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳየው መስፋፋት በቀጣይ በርካታ አካባቢዎችን ያዳርሳል የሚል ስጋት አጭሯል።

2019 ኤን ሲ ኦ ቪ የተሰኘው ቫይረስ ከዚህ ቀደም በሰዎች ላይ ያልታየ መሆኑንም የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የመተንፈሻ አካል ችግር፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ መተንፈስ አለመቻል፣ ሳል እና የትንፋሽ መቆራረጥ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች የሚያሳዩት ምልክት ነው።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.