Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች  ቁጥር ለተካታታይ ሶስት ቀናት ቅናሽ አሳየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ለተከታታይ ሶስት ቀናት ቅናሽ ማሳየቱን አስታወቀች።

የሀገሪቱ ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት በሀገር አቀፍ ደረጃ 2 ሺህ 9 አዲስ የቫይረሱ ተጠቂዎች ሲመዘገቡ 142 ሰዎች ህወይታቸው አልፏል።

ባለፈው ሳምንት ተጠቂዎች የሚቆጠሩበት ሂደት መቀየሩን ተከትሎ የአዲስ ተጠቂዎች ቁጥር ከፍ ብሎ የነበረ ቢሆንም ከዚያን በኋላ እየቀነሰ መምጣቱ ተነግሯል።

አሁን ላይ በቻይና 68 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን የሟቾች መጠንም 1 ሺህ 665 መድረሱን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይፋ አድርገዋል።

ከቻይና ውጭ ደግሞ በ30 ሀገራት 500 የቫይረሱ ተጠቂዎች እንደተመዘገቡ እና አራት ሰዎችም ህይወታቸው እንዳለፈ ተጠቁሟል።

የሀገሪቱ ብሄራዊ የጤና ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሚ ፌንግ ቻይና ÷ እየወሰደችው ያለው እርምጃ በኮሮና ቫይረስ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ ማሳደር ጀምሯል ብለዋል።

የአለም ጤና ድርጅት ሃላፊ ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በትናትናው ዕለት ቻይና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየወሰደች ያለውን እርምጃ አድንቀዋል።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.