Fana: At a Speed of Life!

በነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ ከሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ አሠራር በተመሳሳይ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም እንደሚቀጥል አስታውቋል።

በዚህም በነሐሴ ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ በሐምሌ ወር 2014 ዓ.ም እየተሸጠበት ባለው ዋጋ ያለምንም ለውጥ ይቀጥላል ብሏል።

ሚኒስቴሩ የአውሮፕላን ነዳጅ በወቅታዊ የዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ በመጣው ሂሳብ መሰረት በሊትር 84 ብር ከ42 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ መሆኑንም ነው የገለጸው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.