Fana: At a Speed of Life!

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 29 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ የዓለም አቀፍ ነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ማረጋጊያ ፈንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጉድለት ያስከተለ መሆኑን አስታውቋል።
 
በተጨማሪም የአገር ውስጥ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከጎረቤት አገራት የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እስከ አንድ መቶ ፐርሰንት በማደጉ እና ምርቱ ለከፍተኛ ኮንትሮባንድ የተጋለጠ በመሆኑ እንዲሁም አገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን መከለስ አስፈላጊ በመሆኑ አዲስ የመሸጫ ዋጋ ተዘጋጅቷል ብሏል።
 
በዚህም መሰረት ቤንዚን ላይ በተደረገ የዋጋ ማስተካከያ ባለፈው ወር ሲሸጥበት ከነበረው ዋጋ ጭማሪ በማድረግ በሊትር 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል።
 
እንዲሁም ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ29 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም ይሸጣል ብሏል በመግለጫው።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.