Fana: At a Speed of Life!

በነገው ዕለት የፌዴራል ፓሊስ በመስቀል አደባባይ የሰልፍ ትርኢት የሚያካሄድ ሲሆን በዕለቱ የሚዘጉ መንገዶች እንደሚኖሩ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በነገው ዕለት ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ30 እስከ 6 ሰዓት 30 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የሰልፍ ትርኢት እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን “ከራስ በላይ ለህዝብና ለሀገር” በሚል መልእክት የፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ዝግጁነት የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞችን እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህም ነገ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሰልፍ ትርኢቱ ይካሄዳል፡፡

በዚህ መሰረት 1.ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ

2.ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ፤ ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ

3.ከቦሌ መድሃኒያለም፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ፤

4. ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት የይለፍ ፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

5.በተመሳሳይ ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት አካባቢ፤

6. ከተክለሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

7.ከተክለሀይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር፤

8. ከጌጃ ሰፈር፣ጤና ጥበቃ፣ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

9.ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ፤

10. ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ሜክሲኮ ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት ዝግ መሆኑ ታውቋል፡፡

ለዚህም አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪ ማስተላለፉን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.