Fana: At a Speed of Life!

በኒውክሌር ጣቢያ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ጥቃት ራስን የማጥፋት ድርጊት ነው – አንቶኒዮ ጉተሬዝ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኒውክሌር ግጭት ስጋት ከብዙ አሥርት ዓመታት በኋላ ዳግም መመለሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተናገሩ፡፡

ኒውክሌር የታጠቁ ሀገራት መንግስታትም የጦር መሳሪያውን ቀዳሚ ምርጫቸው እንዳያደርጉም ጠይቀዋል።

በዩክሬን ‘’ዛፖሪዝዢያ’’ በሚባለው የኒኩሌር ጣቢያ ላይ የተኩስ ልውውጦች መደረጋቸውን የገለፁት ዋና ፀሀፊው፥ በኒውክሌር ጣቢያ ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ራስን የማጥፋት ድርጊት ነው ሲሉ በጃፓን ቶኪዮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

የዩክሬን ሀይሎች በሀገሪቱ ደቡባዊ ዛፖሮዢ ክልል የሚገኘውን የኒውክሌር ጣቢያን ባለፈው አርብ ጥቃት ፈፅመዋል ስትል ሞስኮ መክሰሷን ተከትሎ፥ ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአውሮፓ ትልቁ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ሊደርስ የሚችለውን የኒውክሌር አደጋ አሳሳቢነት ገልፀዋል፡፡

ኪየቭ በበኩሏ ሩሲያ ተቋሙን ለወታደሮቿ እንደ ጋሻ እየተጠቀመች ነው ስትል ትከሳለች።

ጉቴሬዝ በቶኪዮ ሁለቱንም ወገኖች ሳይወቅሱ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በኒውክሌር ጣቢያ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ጥቃት ራስን የማጥፋት ድርጊት መሆኑን ተናግረዋል።

ዋና ፀሀፊው ጥቃቶች እንደሚቆሙ እና በተመሳሳይ ጊዜ ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ሀይል ኤጀንሲ በጣቢያው አደጋን ማስቀረት የሚያስችል ቅኝት እንደሚያደርግ ተስፋ አደርጋለሁ ነው ያሉት።

ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ በዛፖሮዢ የኑክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የደረሰው ድብደባ “በጣም አሳስቦኛል” ማለቱን የሲ ጂ ቲ ኤን እና አር ቲ ዘገባዎች አመልክተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.