Fana: At a Speed of Life!

በኒው ዚላንድ የተከሰተው ጎርፍ ከፍተኛ ጉዳት አስከተለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኒውዚላንድ አውሎነፋስ የቀላቀለ ወቅቱን ያልጠበቀ ከባድ ዝናብ ያስከተለው “አስፈሪ ጎርፍ” በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ከቄያቸው ማፈናቀሉ ተነገረ፡፡

ለሶስት ተከታታይ ቀን የዘነበ ከባድ ዝናብ የኒውዚላንድ ደቡባዊ ደሴትን ምዕራባዊ እና ሰሜናዊ ክፍል በጎርፍ በማጥለቅለቅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ሲያስገድድ፥ የመንገድ እና የትምህርት ተቋማት መዘጋት እንዲሁም የመሬት መንሸራተት አስከትሏል።

ለሳምንታት የዘለቀውን እርጥበት-አዘል የአየር ፀባይ ተከትሎ የተከሰተው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ በአገሪቱ ደረቃማ መልክዓ ምድር እየተባባሰ መምጣቱም ነው የተገለፀው።

የመሬት መንሸራተት፣ ዛፎች መገንደስ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋታቸው በደሴቲቱ ሰሜናዊ ክፍል የሚገኙ ነዋሪዎች ከተቀረው አካባቢ እንዲለያዩ አድርጓቸዋል።

አውሎ ነፋሱ አየር መንገዶች በረራዎችን እንዲሰርዙ እና የንግድ ድርጅቶችም እንዲዘጉ ማስገደዱን የዘጋርዲያን ዘገባ አመላክቷል።

በተጨማሪም አንድ ጀልባ ሲያሰጥም፥ መኖሪያ ቤት ጠርጎ መወሰዱምም ተነግሯል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.