Fana: At a Speed of Life!

በኒጀር የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በኒጀር የፕሬዚዳንቱ መኖሪያ አቅራቢያ የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል፡፡

በዋና ከተማዋ ኒያሚ ለ30 ደቂቃዎች የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መካሄዱንም አልጀዚራ ሬውተርስን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ፍራንስ 24 በበኩሉ በሃገሪቱ መፈንቅለ መንግስት መካሄዱን ዘግቧል፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ኒጀር በቅርቡ ምርጫ ማካሄዷ ይታወሳል፡፡

በምርጫውም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ማሃማን ኦስማን ተሸንፈዋል፡፡

ስልጣኑንም የሃገር ውስጥ ሚኒስትር የነበሩት ሞሃመድ ቦዙማ ተረክበዋል፡፡

በዓለ ሲመታቸውንም ከሁለት ቀናት በኋላ ይፈጽማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ማሃማን ኦስማን የምርጫ ውጤቱን ውድቅ ያደረጉት ሲሆን ፍርድ ቤት ለሞሃመድ ባዙም አሸናፊነቱን አጽንቶላቸዋል፡፡

ከቀድሞ ፕሬዚዳንት ሽንፈት በኋላ በሃገሪቱ የታጠቁ ኃይሎች እንቅስቃሴ ማገርሸቱም ተሰምቷል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ እና ሌሎች

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.