Fana: At a Speed of Life!

በኔዘርላንድስ ግማሽ ማራቶን አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኔዘርላንድስ በተካሄደ የሴቶች ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር አትሌት ፀሃይ ገመቹ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌት ፀሃይ ርቀቱን 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ስታሸንፍ፥ አትሌት ታደለች በቀለ ሶስተኛ በመሆን አጠናቃለች።

በተመሳሳይ በስፔኑ ሁዋን ሙጉዬርዛ አመታዊ የግማሽ ማራቶ ውድድር አትሌት ታደሰ ወርቁ በወንዶች ምድብ አሸናፊ ሆኗል።

አትሌት ታደሰ ርቀቱን 31 ደቂቃ ከ39 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት ነው ያሸነፈው።

በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ተካሂዷል።

በውድድሩ በወንዶች ምድብ ካሳዬ አፅብሃ እንዲሁም በሴቶች ምድብ ሃዊ አለሙ አሸናፊዎች ሆነዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.