Fana: At a Speed of Life!

በንግዱ እና በገቢ አሰባሰብ ስርአት ውስጥ የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት እየተሰራ ነው-ወ/ሮ አዳነች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “በንግዱ እና በገቢ አሰባሰብ ስርአት ውስጥ የሚስተዋሉ ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት እና ሁሉም እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ  ስርዓት ለመፍጠር እየተሰራ ነው”   ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የብልፅግና ደጋፊ የሆኑ ንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሄዱ።

እንደሀገርም ሆነ በከተማ ደረጃ በንግድና ገቢ አሰባሰብ ስርአት ውስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የፖርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሁሉም ዜጋ እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበትን  ስርዓት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን  ገልጸዋል ።

ከለውጡ ወዲህ በፌዴራል እና በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከ90 ቢሊየን ብር በላይ የውዝፍ እዳ ምህረት መደረጉን፤ በተጨማሪም በሀገር ደረጃ ከ12 ሺህ በላይ የክስ ፋይሎች መዘጋታቸውንና ከዚህ ውስጥ 6 ሺህ 700 ያህሉ የአዲስ አበባ  መሆኑን ገልጸዋል ።

በንግድ እና ተያያዥ በሆኑ ዘርፎች ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር እና ጀማሪዎችንም እንዲያድጉ ለማድረግ መንግስት በርካታ የመስሪያ እና የመሸጫ ስፍራዎችን በብዛት ይገነባል ብለዋል።

በወንድማማችነትና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር የውስጥም የውጭ ፈተናዎቻችን በጋራ መመከት ያስፈልጋል ያሉት ወይዘሮ አዳነች መጪው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል ።

የንግዱ ማህበረሰብም ከለውጥ ሃይሉ ጎን ቆሞ ለውጥ እንዲመጣ የበኩሉን ጥረት አድርጓል ፤ መንግስትም ለግሉ ሴክተር የሰጠው ትኩረት እጅግ የሚመሰገን ነው ሲሉ በሰጡት የማጠቃለያ አቋም መግለጫ ላይ መግለፃቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለዘመናት ተከማችተው የነበሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ችግሮች ለመፍታት በተወሰደው ሀገር በቀል መፍትሄ ከመንግስት ጎን እንቆማለን፣ ለሃገራዊ ግቦች ስኬት እንተጋለን፣ የሃገራችንን ገጽታ የሚቀይሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ድጋፋችን ይጠናከራል ብለዋል ተወካዮቹ ።

ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር በተካሄደው የምክክር መድረክ በንግድ አሰራር ፣በገቢ አሰባሰብ እና እያጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.