Fana: At a Speed of Life!

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በ2 መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሁለት መኖሪያ ቤቶች ውስጥ የተለያዩ የጦር መሳሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ሃላፊ ኮማንደር አወል አህመድ እንዳስታወቁት በክፍለ ከተማው ወረዳ አንድ በተለምዶ 72 ካሬ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ እና ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ፖሊስ ባደረገው ብርበራ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የተቀመጡ ለጥፋት ዓላማ ሊውሉ የነበሩ ሁለት የእጅ ቦምቦች ተይዘዋል።

በተመሳሳይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል መና ሆቴል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ እና ፖሊስም ጉዳዩን በማጣራት ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው ብርበራ ኡዚ ተብሎ የሚጠራ የጦር መሳሪያ ከሁለት ካርታ እና ከ56 ጥይቶች ጋር እንዲሁም አንድ ኮልት ሽጉጥ ከአራት ጥይቶችጋር፣ 80 የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶች፣ አንድ የጦር ሜዳ መነፅር እና የተለያዩ ሃገራት ገንዘቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር አወል አህመድ አስረድተዋል።

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.