Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ካለፈ አምስት ሰዎች አንዱ አሜሪካዊ መሆኑ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ህይወታቸው ካለፈ አምስት ሰዎች አንዱ አሜሪካዊ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

በዓለም ላይ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 964 ሺህ 839 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ በቫይረሱ ሳቢያ ከሞቱትት ሰዎች መካከል ከአምስቱ አንዱ አሜሪካዊ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ በአሜሪካ እስካሁን በቫይረሱ 199 ሺህ 818 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ ከ6 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

ሀገሪቱ በቫይረሱ ተጽዕኖ ውስጥ ከገቡ የአለም ሀገራት ቀዳሚ ከሆነች መሰነባበቷ የሚታወቅ ሲሆን የአሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል በሀገሪቱ ከ70 በመቶ በላይ በኮቪድ-19 ለህልፈት የሚዳረጉ ሰዎች ዕድሜያቸው ከ65 በላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በዚህም በአሜሪካ በሳምንት በአማካይ 800 ሰዎች በቀን በቫይረሱ ህይወታቸው ሲያልፍ ባሳለፍነው ሳምንት የሟቾች ቁጥር በ5 በመቶ ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡

የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ጤና ኢንስቲትዩት በ2020 መጨረሻ የሟቾች ቁጥር 378 ሺህ እደሚደርስ እና በቀን የ3 ሺህ ሰዎች ህይወት ሊያልፍ እንደሚችል ትንበያውን አስቀምጧል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.