Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ሚሊየን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 30 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ሚሊዮን መሻገሩን መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

እንደ ወርልዶሜትር መረጃ በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 19 ሚሊየን 5 ሺህ 483 የደረሰ ሲሆን÷ በቫይረሱ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 711 ሺህ 858 መድረሱን አመላክቷል፡፡

በቫይረሱ ምክንያትም በአሁኑ ወቅት 65 ሺህ 498 ሰዎች በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን÷ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርም 12 ሚሊየን 192 ሺህ 503 መድረሱን ነው መረጃው የሚያሳየው፡፡

አሜሪካ፣ ብራዚል፣ ህንድ፣ ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ ከአንድ እስከ አምስት በመሆን ወረርሽኙ የጠናባቸው አገራት መሆናቸውን ያመላከተው የወርልዶሜትር መረጃ የቫይረሱ መነሻ የሆነችው ቻይና በሰላሳኛ ደረጃ ተቀምጣለችም ብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.