Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 31 ሚሊየንን ተሻገረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ31 ሚሊየን አልፏል።

በአለም ዙሪያ እስካሁን 31 ሚሊየን 38 ሺህ 922 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተገልጿል።

ከዚያም ባለፈ 962 ሺህ 189 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው አጥተዋል።

እስካሁን ባለው መረጃም 22 ሚሊየን 631 ሺህ 493 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

በአለም በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ ከበረታባቸው አገራት ቅድሚያ የምትይዘው አሜሪካ 6 ሚሊየን 970 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ሲያዙ ከ203 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በተጨማሪም በቅርቡ ቫይረሱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ካለባቸው አገራት ሁለተኛ የተቀመጠችው ህንድ በቫይረሱ የተያዙባት ዜጎቿ ቁጥር ከ5 ሚሊየን 412 ሺህ በላይ ዜጎቿ ከቫይረሱ ሲያዙ ከ86 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

በዚህም በአለም አቀፍ ደረጃ ከአሜሪካ እና ህንድ ቀጥሎ ብራዚል፣ ሩሲያ ፣ ፔሩ፣ኮሎምቢያ ፣ሜክሲኮ፣ደቡብ አፍሪካ፣ስፔይን እና አርጀንቲና ወረርሽኙ የበረታባቸው አገራት በመሆን እስከ አስረኛ ደረጃን መያዛቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

ምንጭ፡- ወርልድ ኦ ሜትር

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.