Fana: At a Speed of Life!

በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ17 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 23፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በአለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ17 ሚሊየን መሻገሩን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ያሳያል፡፡

በወረርሸኙ ከተያዙት ሰዎች በተጨማሪ ከ667 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከ9 ነጥብ9 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋባት ያለችው አሜሪካ እስካሁን ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮናቫይረስ ህይወታቸው ሲያልፍ÷ ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

የአለም ጤና ድርጅት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ “አንድ ትልቅ ማዕበል” ነው ሲል የገለጸው ሲሆን ÷ወረርሽኙ እንደ ኢንፍሉዌንዛ ወቅታዊ አይደለም ማለቱም የሚታወስ ነው ፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.