Fana: At a Speed of Life!

በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሚሊየን ተጠጋ

በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 7 ሚሊየን ተጠጋ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በአለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች 7 ሚሊየን እየተጠጋ መሆኑ ተገልጿል።

በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች በተጨማሪ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም 400 ሺህ መድረሱ ነው የተነገረው።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው ሰዎች መካከል 30 በመቶ ያህሉ ማለትም 2 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በአሜሪካ የሚገኙ ናቸው።

በአምስት ወራት በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዓለም በጣም አደገኛ ከሆኑ ተላላፊ በሽታዎች አንዱ በሆነው በወባ በሽታ በየዓመቱ ከሚሞቱት ሰዎች ጋር እኩል ሆኗል ተብሏል።

በቫይረሱ ሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በአንዳንድ አገራት ለመመርመር የሚያስችል አቅም ባለመኖሩ ከሆስፒታል ውጭ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ተዳምሮ በይፋ ከተመዘገበው 400 ሺህ እንደሚበልጥ ይታመናል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.