Fana: At a Speed of Life!

በአልጀሪያ  የኢትዮጵያ  ኤምባሲ በሁለት የንግድ ከተሞች  የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ማስተዋወቂያ ሥራዎች አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአልጀሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በአልጄሪያ በሚገኙ  ኦራን እና ሙስታጋን  በተባሉ የንግድ ከተሞች የንግድ ፣ የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም ማስተዋወቂያ ስራዎች  አካሂዷል ፡፡

አምባሳደር  ነቢያት ጌታቸው በኢትዮጵያና በአልጄሪያ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንቶች እና ከሌሎች የሁለቱ ከተሞች የስራ ኃላፊዎች ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል ፡፡

አምባሳደሩ  በኢትዮጵያ ስላለው ምቹ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችም  ገለፃ አድርገዋል፡፡

በወቅቱም አምባሳደሩ  የተለያዩ ኩባንያዎችን የመስክ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ÷ጂ.አይ.ኤስ.ቢ  ከተሰኘው በአልጄሪያ ግንባር ቀደም የኤሌክትሪክ ገመድ ማምረቻ ከሆነው ኩባንያ ባለቤቶችና ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በመገናኘት ኢትዮጵያ በዘርፉ ስላለው የኢንቨስትመንት እድል ገለፃ አድርገዋል ፡፡

በተጨማሪም በአገሪቱ ትልቁ የግብርና ኢንዱስትሪ ቡድን ሜቲዲጂ ግሩፕ ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር በመወያየት በአግሮ ቢዝነስ ዘርፍ ኢትዮጵያ ስላላት ትልቅ አቅም አስረድተዋል ፡፡

ሁለቱም ኩባንያዎችም የቅድመ-ኢንቨስትመንት ጉብኝት በኢትዮጵያ ለማድረግ ተስማምተዋል ፡፡

ከዚያም ባለፈ በአልጄሪያ የቱሪስት መዳረሻ ከተሞች አንዷ በሆነችው ኦራን ውስጥ የጉብኝት ኦፕሬተር ከሆኑት የሃያ ቱር ባለሥልጣናት ጋር በተደረገ ውይይት÷ኢትዮጵያን በቱሪስት መዳረሻ ዝርዝራቸው ውስጥ  ለማካተት እና የኢትዮጵያን የቱሪስት መስህቦች ለማስተዋወቅ ስምምነት ላይ  መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.