Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልልና በመተከል ዞን አጎራባች አካባቢዎች የሚታየውን የሰላም እጦት ለመፍታት የሁለቱ ክልል የጋራ ጥምር ኮሚቴ ውይይት አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ በሆኑት በመተከል እና በአዊ ዞን በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ላይ በመምከር አስተማማኝ ሰላም ለማምጣት ጥምር ኮሚቴው ውይይት እካሄደ።

ውይይቱ የአዊ ዞን አዋሳኝ በሆነው የመተከል ዞን በተደጋጋሚ ለሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እልባት ለመስጠት ያለመ መሆኑም ተገልጿል።

በውይይት እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች ሞት፣ መፈናቀልና የንብረት መውደም ለመታደግና መፍትሄ በማስቀመጥ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ መጠናቀቁ ተጠቁሟል።

የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የጸጥታ አካላት እና ቀጠናውን በኮማንድ ፖስት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዛዦች በውይይቱ ላይ መገኘታቸውን የመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.