Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በ2013/14 የመኸር እርሻ ሰሊጥ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ኤልያስ በላይ እንደገለጹት በክልሉ በ2013/14 የመኸር ምርት ዘመን ከ378 ሺህ 440 ሄክታር በሚበልጥ መሬት ላይ የለማው የሰሊጥ ሰብል በወቅቱ ተሰብስቧል።

አቶ ኤሊያስ እንዳሉት በክልሉ አዊ፣ ማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖችን ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ከለማው መሬት ከ2 ሚሊየን 270 ሺህ ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል።

በክልሉ በምርት ዘመኑ ገበያ ተኮር ለሆኑ ሰብሎች ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በዘንድሮው የመኸር እርሻ በሰሊጥ የለማው መሬት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ154 ሺህ ሄክታር ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።

እንዲሁም በምርት ዘመኑ የሚጠበቀው የሰሊጥ ምርት ደግሞ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ732 ሺህ ኩንታል ያህል ብልጫ እንደሚኖረው አስታውቀዋል።

ምርቱ ከብክነት በፀዳ መልኩ እንዲሰበሰብ መደረጉን ጠቅሰው፥ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ ሰሊጥ ለውጭ ገበያ በማቅረብ አገሪቱ የተሻለ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ እየተሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.