Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሁለት መንገዶች ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ3 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በጀት የተያዘላቸው ሁለት መንገዶች ግንባታ ተጀመረ፡፡

የአርብ ገበያ -ሰከላ -ቲሊሊ ሎት ሁለት 62 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እና የደንበጫ – ሰቀላ እና የቢቡኝ አገናኝ ኮንትራት አንድ 70 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በይፋ ተጀምሯል።

የአርብ ገበያ-ሰከላ-ቲሊሊ ሎት ሁለት 62 ኪሎ ሜትር መንገድ በ1 ቢሊየን 673 ሚሊየን 300 ሺህ 137 ብር ወጪ የሚገነባ ነው፡፡

ሁለተኛውና 70 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍነው የደንበጫ-ሰቀላ ቢቡኝ አገናኝ ኮንትራት አንድ መንገድ 1 ቢሊየን 790 ሚሊየን 5 ሺህ 720 ብር የተመደበ ሲሆን፥ ግንባታው አራት አመት ተይዞለታል፡፡

በመንገዶቹ ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርአት ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ደይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝ እና የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሁለቱም መንገዶች ግንባታ ወጪ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን፥ የመንገዶቹ ግንባታ በአካባቢዎቹ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቶቹ ከአዲስ አበባ – ደጀን ደብረማርቆስ – ዳንግላ – ባህርዳር መንገድ እና ከአዲስ አበባ – ደጀን ደብረወርቅ -መርጦ ለማርያም – ባህርዳር የሚዘልቀውን ዋና መንገድ በአቋራጭ የሚያገናኝ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑ ተገልጿል ፡፡

በማህሌት ተክለብርሀን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.